391 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

(አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27/ 2016 ዓ.ም) በሳዑዲ ዓረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ 391 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ።

ዛሬ ወደ ሀገር የተመለሱት 388 ወንዶችና 2 ሴቶቾ ሲሆኑ ከተመላሾች መካከል 13 እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል። ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ የማድረግና ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡ ከሚያዚያ 04 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ በሚገኘው ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ስራ እስካሁን ከ76 ሺህ 500 በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ ተችሏል።

 

Please follow and like us: