670 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

በሳዑዲ ዓረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ 670 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ።

ወደ ሀገር የተመለሱት 662 ወንዶች እና 8 ሴቶቾ ሲሆኑ ከተመላሾች መካከል 12 እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል። ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡ ከሚያዚያ 04 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ በሚገኘው ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ስራ እስካሁን ከ77 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ ተችሏል።

Please follow and like us: