1ሺህ 173 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

በሳዑዲ ዓረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ 1ሺህ 173 ኢትዮጵያውያን በዛሬው እለት ወደ ሀገራቸው ተመለሱ።

በእለቱ ወደ ሀገር የተመለሱት 1ሺህ 144 ወንዶች እና 29 ሴቶች ሲሆኑ ከተመላሾች መካከል 12 እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል። ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ የማድረግ እና ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡

ከሚያዚያ 04 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ በሚገኘው ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ስራ እስካሁን ከ80 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ ተችሏል።

 

Please follow and like us: