በሊባኖስ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያሉ ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ስራ ተጀምሯል

መንግስት እየተከተለ ባለው ዜጋ ተኮር የዲፕሎሚሲ ፖሊሲ መሰረት በእስራኤል የአየር ጥቃት ስር በምትገኘው ሊባኖስ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ስራ ተጀመሯል። በሊባኖስ በጦርነት ቀጠና ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር የመመለስ ስራው ዛሬ ማክሰኞ መስከረም 28 ቀን 2017 ዓ.ም የተጀመረ ሲሆን 49 ሴቶች እና 1 ወንድ በድምሩ 50 ዜጎችን ወደ ሀገር መመለስ ተችሏል።

ተመላሽ ዜጎች ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ከተለያዩ መንግስታዊ ተቋማት በተውጣጡ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች አቀባበል ተደርጎላቸዋል። ዜጎች መንግስት ባመቻቸው አሰራር መሰረት በኤንባሲ በኩል በሚያደርጉት ምዝገባ በሊባኖስ በጦርነት ቀጠና ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን የመመለሱ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል። በሊባኖስ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዜጎቸን የመመለሱ ስራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የአደጋ ስጋትና ስራ አመራር ኮሚሺን ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር እየሰሩ መሆኑ ታውቋል።

Please follow and like us: