ኢትዮጵያ እና ሩዋንዳ ምርጥ ተሞክሮዎችን በመጋራት ዘላቂ የልማት ግቦችን ለማሳካት በትብብር መስራት በሚችሉባቸው ዘርፎች ላይ ተወያዩ::

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) በትላንትናው ዕለት በፅ/ቤታቸው በኢትዮጵያ የሩዋንዳ አምባሳደር ከሆኑት አምባሳደር ቻርለስ ካራምባ ጋር በትብብር ለመስራት የሚያስችላቸውን ፍሬያማ ውይይት አድርገዋል።

በውይይቱ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) እንደገለፁት ኢትዮጵያ እና ሩዋንዳ አምስት አስርት አመታትን ያስቆጠረ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት እንዳላቸው ጠቅሰው ሁለቱ አገራት ያላቸውን ትስስር በማሳደግ ዘላቂ የልማት ግቦችን ለማሳካት በትብብር መስራት እነደሚገባ ጠቅሰዋል ። ሚኒስትሯ እንደገለፁት ሩዋንዳ በጾታ እኩልነት እና የሴቶችን አቅም በማጎልበት የሰራችው ስራ የሚደነቅ መሆኑን ጠቅሰው እነዚህን ተሞክሮዎች ወደ ሀገራችን በማምጣት መስራት እንደሚያስፈልግ ጠቅሰዋል።

በተለይም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በሴቶች ኢኮኖሚ ተጠቃሚነትና የፓለቲካ ተሳትፎ ላይ የጀመራቸውን እንቅስቃሴዎች አጠናክሮ ለመቀጠል እንደ ሩዋንዳ ያሉ አገራትን ተሞክሮ ማየት እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል ። አምባሳደር ቻርለስ ካራምባ በበኩላቸው ሩዋንዳ የሥርዓተ-ፆታ እኩልነትን እና የሴቶችን አቅም በማጎልበት ፣ በተለይም በፖለቲካ ተሳትፎ ላይ የምታደርገው ጥረት ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰው ለዚህም ማሳያ ሁለት ሶስተኛው የፓርላማ መቀመጫ እና 52 በመቶ የካቢኔ ቦታዎች በሴቶች የተያዙ መሆናቸውንም ጠቅሰዋል።

በእነዚህ እና ሌሎች ስራዎች ላይም ከኢትዮጵያ ብሎም ከሚኒስቴር መስሪያቤቱ ጋር በትብብር ለመስራት ከዚህ በዠ፣፣፣፣ፊት ከተደረሱ ስምምነቶች ባሻገር አዲስ የስምምነት ሰነዶችን ከማዘጋጀት ጀምሮ የተለያዩ ዝግጁነቶች መኖራቸውን አምባሳደሩ ገልፀዋል።

Please follow and like us: