እንደዜጋ ብሔራዊ አንድነታችን እንዲጠናከር፣ የሀገራችን ሉዓላዊነት እንዲረጋገጥ፣ ዕድገቷ እንዲፋጠንና በአለም አደባባይ ከፍ ብላ እንድትታይ በየተሰማራንበት መስክ መረባረብ ይጠበቅብናል

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሠራተኞች የዘንድሮው የሰንደቅ ዓላማ ቀን “ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ከፍታ!” በሚል መሪ ሃሳብ ለ17ኛ ጊዜ በተለያዩ መርሀ ግብሮች አከበሩ።
ቀኑን ምክንያት በማድረግ የተቋሙ አመራሮችና ሠራተኞች ረፋዱ ላይ ሰንደቅ ዓላማ በመስቀልና በሰንደቅ ዓላማ ፊት ቃለ መሐላ በመፈፀም እንዲሁም ውይይት በማካሄድ በደማቅ ሁኔታ አክብረዋል። በመርሃ ግብሩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ ክቡር አቶ ጌታቸው በዳኔ ሰንደቅ ዓላማችን የመስዋዕትነት፣ የሉዓላዊነት፣ የአንድነት፣ የነጻነት፣ የታሪክ፣ የአብሮነታችንና የብሔራዊ መግባባት መገለጫ ልዩ አርማ መሆኑን ተናግረዋል።
ለሀገራችን ያለንን ጥልቅ ፍቅርና ክብር የምናሳይበት የብሔር ብሔረሰቦች እኩልነት የተረጋገጠበት በመሆኑ ሁላችንም ለሰንደቅ ዓላማ የሚገባውን ክብር መስጠት ይኖርብናል ብለዋል።
ብሔራዊ አንድነታችን እንዲጠናከር፣ የሀገራችን ሉዓላዊነት እንዲረጋገጥ፣ ዕድገቷ እንዲፋጠንና በአለም አደባባይ ከፍ ብላ እንድትታይ እንደዜጋ ሁላችንም በተሰማራንበት መስክ መረባረብ ይጠበቅብናል ሲሉ አሳስበዋል፡፡
Please follow and like us: