በአማራ ክልል በተፈጠረው ጦርነት እና የድጋፍ ስራዎች ላይ ውይይትና ድጋፍ ተካሄደ

የህውሃት አሸባሪ ቡድን በከፈተው ጦርነት የተፈጠሩ ማህበራዊ ቀውሶች እና የመፍትሄ እርምጃዎች ዙሪያ በአቶ ዘላለም የአማራ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኪምሽን ኮሚሽነር ጥናታዊ ጽሁፍ ቀርቦ ውይይት ተደርጓበታል።ሰነዱን ያወያዩት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ክብርት ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ እንደገለጹት ጦርነት በሚኖርበት ጊዜ ማህበራዊ ቀውስ የሚፈጠር በመሆኑ ቀውሱ እንዳይባባስ ሁሉም ማህበረሰብ በርብርብ በመስራት ማስቆም ይገባል ብለዋል።አክለውም ተፈናቃዮች ከቁሳቁስ ድጋፍ ባለፈ የስነ አእምሮ ድጋፍ የሚያስፈልግ በመሆኑ ከጤና ጥበቃ ጋር በጋራ በመሆን ሊሰራ እንደሚገባ ተናግረዋል።

የክልሉ አመራሮች በበኩላቸው አለም አቀፍ ተቋማት የችግሩ ስፋት ቢረዱትም እስከ አሁን ምንም አይነት ድጋፍ ለማድረግ ፍቃደኞች አለመሆናቸው ገልጸዋል። ተፈናቃዮቹ ምንም እንኳን ከአለም አቀፍ ተቋማት ድጋፍ ባያገኙም ከመንግስትና አጋር ድርጅቶች ከዜጎች የሚሰጠው ድጋፍ በመልከም ሁኔታ ላይ መሆናቸውን ገልፀው በድጋፍ አሰጣጡ ሂደት ላይ የመጠንና ፍጥነት ውስንነት መኖሩንም ተናግረዋል።ጦርነቱ በፈተረው ቀውስ 54,354 ህጻናት፣ 15,251 ሴቶች፣ 7,393 አረጋዊያን 2,023 አካል ጉዳተኞች ልዩ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው መሆኑ በሪፖርቱ ተነስቷል።የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ከበደ በበኩላቸው የወደሙና በከፊል የተጎዱ የጤና ተቋማትን አገልግሎት እንዲሰጡ ለማስቻል ስራዎች እየተሰሩ ቢሆንም ከችግሩ ስፋት አንጻር በፍጥነት ወደ ነበረበት ሁኔታ መመለስ አለመቻሉን ገለጸዋል።ይሁንና አጋር ድርጅቶችን በማስተባበር በፍጥነት ችግሩን በመቅረፍ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማስቻልና መደበኛ የአገልግሎት ስራዎች ላይ ጫና እንዳይፈጥር ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ተናግረዋል።በውይይቱ ላይ የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርእሰ ብሄር ዶክተር ይልቃል ከፋለ፣ ሚኒስትሮች፣ የክልል ቢሮ ሀላፊዎች፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ተወካዮች እና ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተውበታል።በቀጣይም ችግሩ እስኪቀረፍ ለመደገፍ የፌዴራል ተቋማት ከክልል ተቋማት ጋር በተሻለ ቅንጅትና አሰራር በመስራትና ማህበረሰቡን በማነሳሳት ለመርዳትና ለመደገፍ የሚገባንን ሃላፊነት ልንወጣ ይገባናል ተብለዋል።

ከውይይቱ በኋላ ተቋሙ መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ አጋር ድርጅቶች ያሰባሰበውን መድሀኒት፣አልባሳት፣ ብስኩት፣ አልሚ ምግቦች፣ የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ፣ አጎበር፣ የመጠለያ ድንኳን እንዲሁም የሴቶች ንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ 3,616,,615,52 ( ሶስት ሚሊየን ስድስት መቶ አስራ ስድስት ሽህ ስድስት መቶ አስራ አምስት ብር ከአምሳ ሁለት ሳንቲም) የሚገመት ድጋፍ ማድረግ ተችሏል።በእለቱ ከዋግ ህምራ ብሄረሰብ ተፈናቅለው ለሚገኙ ሴቶች ቀጥታ በጥሬ ገንዘብ ብር 110,00000 አንድመቶ አስር ሚሊየን ብር ድጋፍ ተደርጓል። በተጨማሪም ዘንዘልማ አከበቢ የሚገኙ ተፈናቀዮች በአከባቢው በመሄድ የጉብኝት፤ ድጋፍና ማበረታታት መረሃ ግብር በልእኳን ቡድኑ ተደርጓል፡፡በመጨረሻም የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ እና የአማራ ክልል የሴቶች፣ ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሃለፊ ወ/ሮ አስናቁ ደረሰ የገንዘብና የአይነት ድጋፍ ያደረጉትን መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ዩኒሴፍና ስዊዲሽን ከልብ አመስግነዋል።

Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *