“የእህቴ ጠባቂ ነኝ” በሚል መርህ የተዘጋጀ የ16ቱ ቀን የጸረ-ጾታዊ ጥቃት የንቅናቄና ድጋፍ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር ይፋ ተደረገ

 የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከተለያዩ ማህበራትና አጋር አካላት ጋር በመተባበር “የእህቴ ጠባቂ ነኝ” እንዲሁም ሰላም ይስፈን በሴቶችና ሕጻናት ላይ የሚደርስ ጥቃት ይቁም በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ የ16ቱ ቀን የጸረ-ጾታዊ ጥቃት የንቅናቄና ድጋፍ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር በመስቀል አደባባይ ይፋ ተደረገ፡፡ መርሐ ግብሩ ይፋ ሲደረግ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ሴቶች ፎረም አባለትን ጨምሮ የተለያዩ የህብረተሰብ ከፍሎች ተሳትፈዋል፡፡
በእለቱም የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የሴቶችና የህጻናት ዘርፍ ሚኒስተር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አለሚቱ ኡሞድ እንደገለጹት ለተፈናቃይዜጎችና ለመከላከያ ሰራዊታችን ድጋፍ የሚውሉ ደረቅ ምግቦች፣የዱቄት ወተት፣ዘይት፣የንጽህና መጠበቂያና ማብሲያ ቁሳቁሶች፣ የተለያዩ አልባሳት፣ ብርድ ልብሶች፣ አንሶላዎችና ፍራሾች ለማሰባሰብ በትኩረት ይሰራል ብለዋል፡፡
በመርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሴቶች ተወካይ በኢትዮጵያ የሆኑት ሌቲ ቺዋራ በበኩላቸው እንደገለጹት “የእህቴ ጠባቂ ነኝ” በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀው የድጋፍና ንቅናቄ ፕሮግራም በችግር ውስጥ የሚገኙ ሴት የህብረተሰብ ክፍሎችን ለመድረስ በሚደረገው ጥረት ውስጥ የበኩሉን አስተዋጽኦ እንደሚወጣ ገልጸዋል፡፡
የድጋፍ መርሐ ግብሩ ከህዳር 28 እሰከ ታህሳስ 8 የሚዘልቅ ሲሆን የደም ልገሳን ጨምሮ በጦርነቱ ምክንያት ለተፈናቀሉና በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለሚገኙ ሴት የህብረተሰብ ክፍሎች የተለያዩ የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች፣አልባሳትና ምግብ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችና ተቋማት እንደሚሰበሰብ ተገልጸዋል፡፡
Please follow and like us:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *